Posts

ጅማ - ደማችን የፈሰሰባት፣ ድላችንን የተቀማንባት ከተማ!

Image
ውድ የፈረሰኞቹ ገጽ ተከታታዮች ይህ ገጽ ለ 3 አመታት ለቀረቡ ጊዜያት ያህል ቅዱስ ጊዮርጊስን በተመለከተ ዘገባ ሲሰራ በደጋፊዎች መሃል የሚነሱ ግጭቶችን እምብዛም ሽፋን አይሰጥም ነበር። ምክንያቱም ግጭቶቹ እግርኳሳዊ በመሆናቸው እና በአገራችን ሜዳዎች የሚከሰቱ ግጭቶች የተለመዱ እና እግርኳሳዊ ፉክክሮች የሚያስነሳቸው በመሆናቸው ነበር። እንዲሁም የፈረሰኞቹ ገጽ በዳኛ ውሳኔ ላይ በፍፁም አስተያየት ሰጥቶ አያውቅም። በተጨማሪም በዳኛ ውሳኔ ላይ ግላዊ አሰተያየቶችን በገፃችን ላይ አቅርበን አናውቅም። ምክንያታችንም የዳኛ ስህተት የእግርኳስ የጨዋታ አካል በመሆኑ እንዲሁም ስህተቶች ያሉ እና የሚኖሩ በመሆናቸው ብቻ ነበር። ሆኖም በጅማ ስታዲየም የተከሰተው ፍፁም ከእግርኳስ መሰረታዊ መርህ ያፈነገጠ፣ በእግርኳስ ሜዳ ሊከሰት የማይገባው እና የፈረሰኞቹ ገጽ እንደ አንድ የስፖርቱ ባለድርሻ አካል የምናወግዘው በመሆኑ የተፈጠሩ ሁነቶችም አንድ ሁለት ብለን ልንናገር ወደድን።   በጅማ ስታዲየም የመጀመሪያው ችግር የተከሰተው የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ወደ ጅማ ከተማ ሲደርሱ ነው። ደጋፊዎቹ በአውቶብሶቻቸው ላይ ሆነው እየዘመሩ ወደ ጅማ ከተማ ሲገቡ ከከተማው ነዋሪዎች የጠበቃቸው ነገር አስደንጋጭ ነበር። « አሸንፋችሁን ከዚህ ከተማ በሰላም እንወጣለን ብላችሁ ካሰባችሁ የዋሆች ናችሁ » የሚሉ ድምፆች በርካቶች ናቸው። ከአዲስ አበባ ወደ ጅማ ከተጓዙ አውቶብሶች መካከል በ 1 አውቶብስ ላይ ድንጋይ ሲወረወር የፈረሰኞቹ

በፖለቲካ የተዋጠው፣ የፖለቲከኞች እጅ የተጫነው እግርኳሳችን! - በፈረሰኞቹ ገጽ

Image
ያለፉት አመታት የኢትዮጵያ እግርኳስ የክለቦች ውድድር እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተመሳሳይ ቅኝቶችን ይዘዋል፡፡ ፖለቲካው ሲያቃጥል እግርኳሱ ይግላል፡፡ ፖለቲካው ሲግል እግርኳሱ ለብ ይላል፡፡ በፖለቲካ መሪዎች የሚሰጡ ፖለቲካዊ ውሳኔዎች እግርኳስ ሜዳ ላይ አሻራቸውን በተዘዋዋሪ ያሳርፋሉ፡፡ በእግርኳስ ሜዳ ላይ የሚታዩት ዘረኝነት፣ ወዳጅነት፣ ህብረት እና ክፍፍሎች በተዘዋዋሪ ፖለቲካው መንደር ላይ ቀድመው ይታያሉ፡፡ በእርግጥ ይህ በአለም የእግርኳስም ሆነ የፖለቲካ አካሄድ ላይ እንግዳ ነገር አይደለም፡፡ የእግርኳስ ስታዲየሞች ፖለቲካዊ ድጋፍ እና ተቃውሞ ማስተናገጃ ሆነው ያውቃሉ፡፡ ክለቦች በፖለቲካ አካሄዶች ሲጠለፉም ይታያል፡፡ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ባለባቸው አገራቶች ውስጥ ይህ አይነት አካሄዶች መታየታቸው ይታወሳል፡፡ ሆኖም በዚህ አይነት አካሄድ የተጓዙ አገራት ለእግርኳሳቸው ያተረፉት አንዳችም እምርታ የለም፡፡ እግርኳሱን ወደ ኋላ ጎትተው ጣሉት እንጂ ቀና አላደረጉትም፡፡ እግርኳስን ለፖለቲካ መጠቀሚያ ፍጆታቸው አዋሉት እንጂ እግርኳስ ከፖለቲካው ያተረፈው ነገር የለም፡፡ በወታደራዊው አገዛዝ ዘመን ይህ አይነት አካሄዶች በስታዲየሞቻችን ውስጥ ታይተው ነበር፡፡ በአገሪቱ ውስጥ የተከሰተው የተቃውሞ አመጽ እግርኳሱን ጠልፎት እንደነበር ይታወሳል፡፡ በወታደራዊ ክለቦች እና በህዝባዊ ክለቦች መካከል በአገሪቱ ውስጥ ያለው የፖለቲካ ትኩሳት እጁን አሳረፈበት፡፡ ወታደራዊው ክለብ የወታደሩ፣ ህዝባዊ ክለቦች የተቃዋሚዎች መሳሪያ መሆናቸው ይታወሳል፡፡ ሆኖም በወቅቱ የነበረው የፖለቲካ አስተሳሰብ ብሔርን፣ ሐይማኖትን እና መሰል ልዩነቶች የተከሰተበት አልነበረም፡፡ ልዩነቶቹ በፖለቲካ አስተሳሰብ እና በርዕዮተ ዓለም መለያየት ላይ ያጠነጠኑ ነበሩ፡፡ ይህ ልዩነት የእግርኳስ

It's Match Day!

Image
In Ethiopia, where everything is a challenge, among few things that remained real is St George. St George did not become a history. It did not stop on "it was". It is only our St George that is still on a route it created yesterday before ages. Many clubs could not stand founded later than St George and on better times.  We have a club founded at Arada by youngsters who were ahead of time.   When football was new to Ethiopia, it was us who made the Ethiopian football carrying goal posts from fields to fields, making lines with chalks, wearing sweater as jersey and paid popcorn as a signing fee of players. We thought football's ''A B C D'' spending from our pockets. When Blacks and Whites were different teams because of color, we stood for the impossible, humanity. Using football for freedom, we waved the Green-Yellow-Red flag on Addis Ababa before Emperor HaileSilassie the First and declared our freedom. We are champions of Ethiopian Pre

የፈረሰኞቹ ገጽ ‏- ዛሬ የጨዋታ ቀን ነው!

Image
መውጣትና መውረድ ባለባት ኢትዮጵያ ውስጥ ካልከሸፉ እውነታዎች ውስጥ አንዱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው። ቅዱስ ጊዮርጊስ ታሪክ ሆኖ አልቀረም። «ነበር» በሚባል ቃል ያላበቃ ክለብ ነው። ከዘመናት በፊት፣ ከዘመናት በኋላ፣ ትላንትም ሆነ ዛሬ ባሰመረው መስመር እየተጓዘ የሚገኘው የእኛ ቅዱስ ጊዮርጊስ ብቻ ነው። ከቅዱስ ጊዮርጊስ በኋላ ተመስርተው ያልፀኑ፣ በተሻለ ዘመን ተነስተው በእግራቸው ያልቆሙ ክለቦች እልፍ ናቸው። ዘመናቸውን የቀደሙ፣ ነገን ቀድመው በተረዱ ወጣቶች አራዳ ላይ በአራዳዎች የተመሰረተ ክለብ አለን። እግር ኳስ በኢትዮጵያ እንግዳ በነበረበት ጊዜ ከሜዳ ሜዳ አንግል እየተሸከምን፣ በኖራ መስመር ሰርተን፣ ሹራብ እንደ ማልያ ለብሰን፣ ተጨዋቾችን ለማስፈረሚያ ቆሎን እንደ ክፍያ ሰጥተን የኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክን ጠፍጥፈን የሰራን እኛ ነን። ከኪሳችን ገንዘብ እያዋጣን የእግር ኳስን «ሀ፣ ሁ» ያስተማርን ቀዳሚዎች እኛ ነን። ነጭና ጥቁር በቀለማቸው ብቻ በተቦደኑት በዚያ ጊዜ የማይሞከረውን እንዲሆን በማድረግ በሰብአዊነት የቆምን እኛ ነን። እግር ኳስን ለሀገራዊ ነፃነት እንቅስቃሴ በማዋል ከንጉሥ ኃይለሥላሴ ቀድመን አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማን በአዲስ አበባ አውለብልበን ነፃነታችንን ያረጋገጥን እኛ ነን። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለ14 ጊዜ ዋንጫ ወስደናል። ውድድሩ እንደ አዲስ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለብቻችን በፍፁም የበላይነት የከበርን እኛ ብቻ ነን። ሀገራችንን በተደጋጋሚ በአፍሪካ መድረክ በመወከል ስማችንን በጉልህ የፃፍን፣ ለአራት ተከታታይ አመታት ማንንም ጣልቃ ሳናስገባ የሊጉን ዋንጫ ያነሳን እኛ ብቻ ነን። በሊጉ ውድድር ያለምንም ሽንፈት ዋንጫ አንስተን የማይቻለውን ችለን ያሳየን እኛ ብቻ ነን። የአዲስ አበባ

በሚዲያ አጠቃቀም የኋልዮሽ ጉዞ ላይ ያለው ቅዱስ ጊዮርጊስ!

Image
ቅዱስ ጊዮርጊስ በአህጉራዊ ውድድሮች ላይ ውጤት በማምጣት ጭምር እየተሳተፈ ይገኛል፡፡ ባሳለፍነው ዓመት ከአፍሪካ ታላላቅ ክለቦች ጋር ጨዋታዎችን ማድረግ ችለናል፡፡ ከታላላቅ ክለቦች ጋር ስንጫወት ከእግር ኳሱ ጎን ለጎን የምንቀስማቸው አስተዳደራዊ እና መሰል ተግባራት ሊኖሩ ይገባል፡፡ ባሳለፍነው ዓመት ቅዱስ ጊዮርጊስ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ድልድል ውስጥ ገብቶ ጨዋታዎችን ሲያደርግ የነበረው የሚዲያ አጠቃቀም ደካማ ነበር፡፡ ሆኖም የፈረሰኞቹ ገጽ በዚያ ወቅት አንድም ነገር ለመናገር አልወደድንም ነበር፡፡ ምክንያታችን የነበረው ለውድድሩ እንግዳ ከመሆን የመነጨ ነው በሚል ነበር፡፡ ይህ ከያዝነው ውድድር ዓመት አንስቶ ይስተካከላል ብለን ተስፋ አድርገን ነበር፡፡ ሆኖም ግምታችን ትክክል አልነበረም፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬም በሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ እጅግ ደካማ ክለብ መሆኑን በተግባር እያሳየ ይገኛል፡፡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ምስረታ ከረጅም አመት በኋላ የተመሰረቱ ክለቦች ከቅዱስ ጊዮርጊስ የተሻለ ሲንቀሳቀሱ እየታዘብን እንገኛለን፡፡ በምስራቅ አፍሪካ ያሉ ብዙም በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የመሳተፍ ታሪክ የሌላቸው ክለቦች ከቅዱስ ጊዮርጊስ እንደሚሻሉ እያየን ነው፡፡ ለዚህም ማሳያዎችን እንጥቀስ፡፡ 1. የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ይፋዊ ድረ ገጽ! ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተወሰኑ ዓመታት በፊት የራሱን ድረ ገጽ ከፍቶ መረጃዎችን ያስተላልፍ ነበር፡፡ ምንም እንኳ ድረ ገጹ ዘመናዊነት ያልተከተለ ቢሆንም ጥረቶቹ ግን የሚያበረታቱ ነበሩ፡፡ ይህ ድረ ገጽ አሁን ላይ አገልግሎት አይሰጥም፡፡ ከዓመታት በፊት የተሰጡትን መረጃዎች ይዞ ተቀምጧል፡፡ በአሁን ሰዓት የድረ ገጹ የደረጃ ሰንጠረዥ ማሳያ እያሳየው የሚገኘው የ2008 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የደረጃ